በዛሬው እለት ነሃሴ 30/2013 ዓ.ም የቀብሪ ደሃር ዩኒቨርሲቲ ለሁለተኛ ጊዜ 821 ተማሪዎችን ያስመረቀ ሲሆን ከነዚህም 520 ወንዶች እና 301 ሴቶች ናቸው።
የምረቃ ስነ-ስርዓቱ የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝደንት ኢንጅ. አብዲፈታህ አህመድ የመክፈቻ ንግግር በማድረግ ያስጀመሩ ሲሆን በመቀጠልም የንግድ ሚንስቴር ደኤታና የቀደዩ ቦርድ ሰብሳቢ አቶ እሸቴ አስፋው፣ የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ደኤታ ዶ/ር ሳሙኤል ክፍሌ በመጨርሻም የሶማሌ ክልል ም/ርእሰ መስተዳድር አቶ ኢብራሂም ኡስማን ለተማሪዎች አበረታች መልእክት ከአደራ ጭምር አስተላልፈዋል።
የምረቃ ስነ-ስርዓቱ ላይ የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር አመራሮች፣ የቦርድ አባላት፣ የሶማሌ ክልል ከፍተኛ አመራሮ፣ ክቡር ዶ/ር አርቲስት አሊ ቢራና ሌሎች ግብዣ የተደረገላቸው የህብረተሰብ ክፍሎች ታድመዋል።
ቀደዩ ነሀሴ 30/2014 ዓ.ም