በቀብሪ ደሃር ዩኒቨርሲቲ ሲሰጥ የቆየው የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ብሔራዊ የሶሻል ሳይንስ ፈተና በሰላም ተጠናቀቀ

በቀብሪ ደሃር ዩኒቨርሲቲ ከክልሉ የተለያዩ 5 ዞኖች የተውጣጡ ከ5,300 በላይ የሆኑ የሶሻል ሳይንስ ተማሪዎች ከመስከረም 30 – ጥቅምት 02/2015 ለ3ቀናት ሲወስዱ የቆየው የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ብሔራዊ ፈተና በሰላም ተጠናቀቀ።

በቀብሪ ደሃር ዩኒቨርሲቲ ሲሰጥ የቆየው የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ብሔራዊ ፈተና በእቅዱ መሰረት በሰላም እንዲጠናቀቅ የዩኒቨርሲቱው ከፍተኛ አመራርና የዩኒቨርሲቱው ማህበረሰብ በሙሉ፣ የቆራሄይ ዞን የቀብሪ ደሃር ከተማ መስተዳድርና ወረዳ፣ የክልሉ መስተዳድር፣ የፌድራል መንግስት ተቋማት፣ የፌድራልና የክልሉ የፀጥታ አካላት እንዲሁም የከተማው ማህበረሰብ (ወጣቶች፣ የሀገር ሽማግሌዎችና ኡጋሶ) ከፍተኛ ተስትፎና ቅንጅታዊ ስራ በመሆኑ ዩኒቨርሲቲው ለሁሉም አካላት ምስጋናውን ያቀርባል።

ቀደዩ ጥቅምት 02/2015

==============================

Jaamacadda Qabridahar: Imtixaanka heer qaran ee fasalka 12aad ka oo maalmahan arday dhan 5,300 oo ka kala yimid 5 gobol ay imtixaan ku qaadanayeen ayaa si nabadgelyo ah ku soo dhamaaday.

Waxaa si habsami leh ku soo dhamadaay imtixaanka shahaadada ah ee heer qaran ee fasalka 12aad-ka gaar ahaan ardayda baratay cilmiga arrimaha bulshada.

Jaamacadda Qabridahar, maamulka gobolka Qorraxay, maamulka magaalada iyo hay’adaha amniga heer deegaan & heer qaran ayaa si wadajir ah uga qaybqaatay geeddi-socodka imtixaanka oo si nabdoon ku soo idlaaday.

Uok