በቀብሪ ደሃር ዩኒቨርሲቲ ከክልሉ የተለያዩ 5 ዞኖች የተውጣጡ ከ6,000 በላይ የሆኑ የናቹራል ሳይንስ ተማሪዎች ከጥቅምት 8- 11/2015 ለ4ቀናት ሲወስዱ የነበረው የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ብሔራዊ ፈተና በሰላም ተጠናቀቀ።
ፈታናውን ያጠናቀቁ ተማሪዎች ወደ መጡበት አከቢና ቤተሰቦቻቸው በሰላም እየወጡ ይገኛሉ።
ከተለያየ አከባቢና ዩኒቨርሲቲ ለመጡ የፈተና አስፈፃሚዎች እና የፀጥታ አካላት ዩኒቨርሲቲው የእራት ግብዣ በማድረግ ከምስጋና ጋር ደማቅ የሆነ የሽኝት ፕሮግራም አድርጎላቸዋል።
በዩኒቨርሲቲው ሲሰጥ የቆየው የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ በሔራዊ ፈተና በእቅዱ መሰረት በሰላም እና ባማረ ሁኔታ እንዲጠናቀቅ የዩኒቨርሲቱው ከፍተኛ አመራርና የዩኒቨርሲቱው ማህበረሰብ በሙሉ፣ የቆራሄይ ዞን የቀብሪ ደሃር ከተማ መስተዳድርና ወረዳ፣ የክልሉ መስተዳድር፣ የፌድራል መንግስት ተቋማት፣ የፌድራልና የክልሉ የፀጥታ አካላት፣ የከተማው ማህበረሰብ (ወጣቶች፣ የሀገር ሽማግሌዎችና ኡጋሶ) እንዲሁም ከተለያየ አከባቢና ዩኒቨርሲቲ የመጡ የፈተና አስፈፃሚዎች ከፍተኛ ተስትፎና ቅንጅታዊ ስራ በመሆኑ ዩኒቨርሲቲው ለሁሉም አካላት ላቅ ያለ ምስጋናውን ያቀርባል።
ቀደዩ