በቀብሪደሃር ዩኒቨርሲቲ ከመምህራን እና ከተማሪዎች ጋር የ2015 ዓ.ም የመዉጫ ፈተናን አስመልክቶ ገለፃና በቀሪ ስራዎች ዙሪያ ዉይይት ተካሄደ

በዩኒቨርሲቲዉ ላለፉት ሁለት ቀናት ከተማሪዎች ጋር በዋናነት በዩኒቨርሲቲዉ አካዳሚክ ጉዳዮችና ምርምር ም/ፕሬዝደንት በረ/ፕ አብዲሰላም አብዲላሂ መሀመድ እና በመውጫ ፈተናው ኮሚቴ አባላት የሚመራ የገለፃ እንዲሁም በቀሪ ስራዎች እና ተግዳሮቶች ዙሪያ ውይይት የተካሄደ ሲሆን በዕለቱ ሁሉም ባለድርሻ አካላት ተሳትፈዋል፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለ ከሁለት ቀናት ከተማሪዎች ውይይት በኋላ ከአካዳሚክ ሰራተኞች ጋር የአንድ ቀን ወርክሾፕ የተዘጋጀ ሲሆን በእለቱም የመውጫ ፈተናውን መሰረት ያደረጉ አንኳር አንኳር ጥያቄዎችና ሀሳቦች ተነስተው ውይይት ተደርጎባቸዋል።

ሶስት ቀን በፈጀዉ ወርክሾፕ ላይ በዩኒቨርሲቲው የመውጫ ፈተና ኮሚቴ አባል በሆኑት በረ/ፕ ክበበው ባበጌ ወልደየስ የመነሻ ሀሳብ እና ገለፃ የቀረበ ሲሆን በውይይቱ የሚመለከታቸዉ አካላት ሁሉ የየእራሳቸው ሀላፊነት በመውሰድ በ2015 ዓ.ም በሚሰጠው የመዉጫ ፈተና ዩኒቨርሲቲው ውጤታማ ርብርብ ማድረግ እንደሚገባ የጋራ መግባባት ላይ በመድረስ ውይይቱ በስኬት ተጠናቋል፡፡

ቀብሪደሃር ዩኒቨርሲቲ

የካቲት 03፤2015 ዓ.ም