እንኳን ደስ አለን፤ እንኳን ደስ አላችሁ!
በቀብሪ ደሃር ዩኒቨርሲቲ በአጠቃላይ መደበኛ እና መደበኛ ባልሆኑ ፕሮግራሞቹ ያስፈተናቸው የተማሪዎች ብዛት 1087 ሲሆኑ የዚህም አጠቃላይ የማለፍ ምጣኔ 71.5% በመሆን ተመዝግቧል።
የቀብሪ ደሃር ዩኒቨርሲቲ ካስፈተናቸው 17 የትምህርት ክፍሎች ውስጥ 6 የትምህርት ክፍል ተማሪዎቻችን 100% እንዲሁም 3 የትምህርት ክፍል ተማሪዎቻችን ከ90% በላይ የሆነ ውጤት በማስመዝገብ ማለፍ ችለዋል።
በመሆኑም ተማሪዎቻችን ይህንን ውጤት እንዲያስመዝግቡ ያላሰለሰ ጥረት ያደደረጋችሁ የዩኒቨርሲቲያችን እንቁ መምህራኖች፣ የውጤቱ ባለቤት የሆናችሁ ተማሪዎቻችን፣ በየደረጃው ያሉ የዩኒቨርሲቲያችን ማኔጅመንት ፣ አጠቃላይ የዩኒቨርስቲው ማህበረሰብ እና የአከባቢው ማህበረሰብ በሙሉ በድጋሚ እንኳን ደስ አለን ፤ እንኳን ደስ አላችሁ!
ተማሪዎቻችን ውጤታችሁን #ከእሁድ ማታ ጀምሮ ለፈተናው የተሰጣቸውን #UserName በመጠቀም በዚህ ሊንክ https://result.ethernet.edu.et/ ገብታችሁ ማወቅ ትችላላችሁ።
ቀብሪ ደሃር ዩኒቨርሲቲ
ሀምሌ 08/2015 ዓ.ም