የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ የጉባኤው ማጠናቀቂያ ላይ መልዕክት ያስተላለፉ ሲሆን በመልእክታቸውም፡-
“ሀገርን ለማዳን የተከፈለውን መሥዋትነት የትምህርት ሥርዓቱን በማሻሻል መድገም ይገባናል” ብለዋል።
በመሆኑንም የአንድ ቢሮ ኃላፊ ወይም ዩኒቨርስቲ ፕሬዚዳንት ኅላፊነት ብቁና ጥሩ ዜጎችን ማፍራት የሚያስችል ሥራ መሥራት መሆኑን አውቆ ኃላፊነቱን መወጣት አለበት ብለዋል።
አክለውሞ የትምህርት ሥርዓቱ ላይ ያሉ ችግሮችን በተናጥል በሚደረግ ጥረት መፍታት አይቻልም ያሉ ሲሆን ለዚህም ሁሉም በሚችለው ልክ ዘርፉን እንዲደግፉ ጥሪ አቅርበዋል።
ጉባኤው በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ሲመክር የቆየ ሲሆን የትምህርት ጥራትን ለማረገገጥ እና ብቁና ተወዳዳሪ የሰው ሀይል መፍራት በሚቻላቸው ጉዳዮች ላይ መግባባት ደርሷል።
31ኛው ሀገር አቀፍ የትምህርት ጉባኤ መጠናቀቅን ተከትሎ በ2014 ዓ.ም የኢትዮጵያ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት መልቀቂያ ፈተና አሰጣጥ ሂደት ውስጥ ከፍተኛ አስተዋጾ ላበረከቱ የፀጥታ አካላትን፣የትምህርት ቢሮዎች ፣ዩኒቨርሲቲዎች እና ሌሎች በሂደቱ አበርክቶ ለነበራቸውን ተቋማት የምስጋና እና የእውቅና የመስጠት መርሃ ግብር ተከናውኗል።
ከዚሁ ጋር በተያያዘ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ በፈተና ዝግጅትና አፈጻጸም ሂደት ወቅት ለጥያቄዎቻችን አፋጣኝ ምላሽ በመስጠት ላደረጉልን ድጋፍ እናመሰግናለን ብለዋል።
በመጨረሻም በፈተና አሠጣጥ ሂደቱ ወቅት አበርክቶ ለነበራቸው ተቋሟት የእውቅና ሠርተፍኬት ተሰጥቷል።
ቀደዩ
ህዳር 10/2015 ዓ.ም