“በሀገር ግንባታ የምሁራን ሚና “ በሚል ርዕስ በቀብሪ ደሃር ዩኒቨርሲቲ የተዘጋጀው የምክክር መድረክ በዛሬው ዕለት ተጀመረ

The 2nd day of the panel discussion entitled: “The Role of Intellectuals and Scholars in Our Country’s Nation Building” is smoothly going on at University of Kebridahar Senate Meeting Hall.

በሀገር ግንባታ የምሁራን ሚና “በሚል ርዕስ በቀብሪ ደሃር ዩኒቨርሲቲ የተዘጋጀውና ከታህሳስ 21-24/2015 ዓ.ም ድረስ የሚካሄደው የምክክር መድረክ በዛሬው ዕለት በይፋ ተጀምሯል፡፡

በምክክር መድረኩ ላይ ተገኝተው የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት ክቡር አቶ እንዳለው መኮንን የኢፌዴሪ የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር ሚኒስትር ደኤታና የቀብሪ ደሃር ዩኒቨርሲቲ የስራ አመራር ቦርድ ሰብሳቢ ባስተላለፉት መልዕክት ምሁራን በሀገሪቱ ዘላቂ ሰላም፣ልማትና ዕድገትን ለማስፈንና የጋራ ጉዳዮችን ለማጉላት በሀገረ-መንግስት ግንባታ ላይ የአንበሳውን ድርሻ እንደሚወስዱ ገልጸው ሃሳቦችን ሳይንሳዊ በሆነ መንገድ ምክክር በማድረግ ሀገራችን ኢትዮጵያ የሚገዳደሯትን ችግሮችን መፍታት የሚቻለው ምሁራንን የስራው አካል በማድረግ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

የሀገር ግንባታ በምሁራን ንቁና ጠንካራ ተሳትፎ ሊመራ እንደሚገባ በመታመኑም መንግስት በአገር አቀፍ ደረጃ ከምሁራን ጋር በመምከር እየሰራ እንደሚገኝም አስታውሰዋል።

ሀገራት ያደጉትና የበለፀጉት በምሁራን ሀሳብ አመንጭነት መሆኑን አመልክተው ምሁራን በመወያየትና መግባባት በመፍጠር በኩል ሚናቸውን ሊጫወቱ እንደሚገባ አስገንዝበዋል።

ኢትዮጵያ ታላቅ የስልጣኔና የነፃነት ምልክት መሆኗን፤ አሁንም ሰላማዊና የበለፀገች ሀገር እንድትሆን ሁሉም ምሁር ሀሳብ በማፍለቅ የድርሻውን ሊወጣ እንደሚገባ አስገንዝበዋል።

የምክክር መድረኩም ምሁራን በኢትዮጵያ ዘላቂ ሰላምና ጠንካራ ሀገረ መንግስት ግንባታ ላይ ለውጥ ለማምጣት የሚያስችሉ ሀሳቦችን የሚያፈልቁበት እንደሚሆን ገልጸዋል።

ውይይቱ ለሚቀጥሉት ሶስት ተከታታይ ቀናት የሚቀጥል ሲሆን በዚሁ የምክክር መድረክ ላይ የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚንስትር ሚኒስቴር ደኤታን ጨምሮ ሁሉም የዩኒቨርሲቲው ከፍተኛ አመራሮች እና የስራ ሀላፊዎች በመሳተፍ ላይ ይገኛሉ።

ቀደዩ

ታህሳስ 21/2015 ዓ.ም