“በሀገር ግንባታ የምሁራን ሚና “ በሚል ርዕስ በቀብሪ ደሃር ዩኒቨርሲቲ የተዘጋጀው የምክክር መድረክ በዛሬው ዕለት ተጠናቀቀ

የውይይት መድረኩን በዋና አወያይነት የመሩት የኢ.ፌ.ዴ.ሪ የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር ሚኒስትር ደኤታና የቀብሪ ደሃር ዩኒቨርሲቲ የስራ አመራር ቦርድ ሰብሳቢ የሆኑት ክቡር አቶ እንዳለው መኮንን ሲሆኑ ባስተላለፉት መልዕክትም ምሁራን በሀገሪቱ ዘላቂ ሰላም፣ልማትና ዕድገትን ለማስፈንና የጋራ ጉዳዮችን ለማጉላት በሀገረ-መንግስት ግንባታ ላይ የአንበሳውን ድርሻ እንደሚወስዱ ገልጸው ሃሳቦችን ሳይንሳዊ በሆነ መንገድ ምክክር በማድረግ ሀገራችን ኢትዮጵያ የሚገዳደሯትን ችግሮችን መፍታት የሚቻለው ምሁራንን የስራው አካል በማድረግ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

ምሁራኑ ላነሷቸው ጥያቄዎችና አስተያየቶች ምላሽ የሰጡት ክብርት ሚንስትሩ መንግስት የምሁራኑን በሀገራዊ እድግት ሂደት ውስጥ ተሳትፏቸውን ለማሳደግ ከመቼው ጊዜ በበለጠ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ መሆኑን ጠቅሰው በተለይም ምሁራኑ ይህንን ከሀገርና ከህዝብ የተጣለባቸውን ኃላፊነት መወጣት እንዲችሉ የምሁራኑ ህይወት እንዲሻሻል የአጭር ፣ የመካከለኛ እና የረጅም ጊዜ እቅዶችን በመንደፍ የተለያዩ እንቅስቃሴዎችን ማድረግ መጀመሩን ተናግረዋል፡፡

በመጨረሻም ምሁራኑ በነበራቸው ቆይታ አገር ያለችብትን አሁናዊና ትክክለኛ ነባረዊ ሁኔታ ሰፊና ተጨባጭ ገለፃ የተደረገላቸው በመሆኑ ይህንኑ ግንዛቤ ወስጥ በማስገባት አገርና ህዝብ ከእነሱ የሚጠብቀውን ከመቼው ጊዜ ከፍ ባለ ደረጃ ለመወጣት ዝግጁ መሆናቸውን በውይይት መድረኩ ማጠቃለያ ላይ አረጋግጠዋል፡፡

“በሀገር ግንበታ የምሁራን ሚና” በሚል ርዕስ በየደረጃው ከሚገኙ ቀብሪ ደሃር ዩኒቨርሲቲ ከፍተኛ አመራሮች፣ ምሁራን፣ የአስተዳደርና ድጋፍ ሰጪ የስራ ሃላፊዎች ጋር የነበረው ውይይት መድረክ በመርሃ-ግብሩ መሰረት በጥሩ ሁኔታ መጠናቀቁን ለመረዳት ችለናል፡፡

ቀደዩ