የቦርዱ ሰብሳቢ ክቡር አቶ እሸቱ ወ/ሀዋርያት (የንግድና ኢንደስትሪ ሚኒስተር ደኤታ) የመክፈቻ ንግግር በማድረግ ስብሰባው ያስጀመሩ ሲሆን በማስቀጠልም አጀንዳዎችን በማስቀመጥ ለውይይት ቀርበዋል።
2ኛ. የ2013 ዓ.ም እቅድ ገምግሞ ማጽደቅ
3ኛ. በኮሮና (Covid-19) ጊዜና ድህረ-ኮሮና (Post-Covod-19) የመማር ማስተማርን ለማስቀጠል የተዘጋጀ ልዩ እቅድ ገምግሞ ማጽደቅ
4ኛ. የኮሮና ወረርሺኝን (Covid-19) በመቋቋም የትምህርትና ስልጠና ተግባራትን ለማከናወን የዝግጅት ምእራፍ አፈፃፀም በመጠይቁ መሰረት ገምግሞ ማጽደቅ
5ኛ. የተጔደሉ የዩኒቨርሲቲውን ከፍተኛ አመራሮች ማሟላት
6ኛ. የተጔደሉ የቦርድ አባላትን ማሟላት
በዚሁ መሰረት ውይይት ከተደረገባቸው በኋላ ሪፓርትና እቅዶችን በሙሉ ድምጽ በማጽደቅ እንዲሁም የቅድመ ዝግጅት ስራው አጥጋቢ በመሆኑ ዩኒቨርሲቲው MoSHE በሚያወጣው ካላንደር መስረት ተማሪዎችን በመጥራት የመማር ማስተማር ስራውን እንዲጀምር ተወስኗል።
በመቀጠልም
1ኛ. ኢን. አብዲፈታህ አህመድ ራቢ – ተጠባባቂ ፕሬዝደንት
2ኛ. አቶ በሺር ዩሱፍ ፉራህ – የአስተዳደርና ልማት ም/ፕሬዝደንት
3ኛ. አቶ አብዲሰላም አብዱላሂ መሀመድ – የአካዳሚክ ጉዳዬች ም/ፕሬዝደንት
4ኛ. አቶ አህመድ ሙሁመድ አብዲናሲር – የምርምርና ማህበረሰብ አገልግሎት ም/ፕሬዝደንት ሆነው እንዲያገለግሉ በሙሉ ድምጽ የተወሰነ ሲሆን ሁለት (2) የተጔደሉ የቦርድ አባላትም ተሰይመዋል።
ቀደዩ
መስከረም 25 ቀን 2013 ዓ.ም