በቀብሪዳሃር ዩኒቨርሲቲ የምርምር፣ ሕትመትና ቴክኖሎጂ ሽግግር ዳይሬክቶሬት ከድህረ ምረቃ ጥናት ዳይሬክቶሬት ጋር በመተባበር ተዘጋጅቶ
ለድህረ ምረቃ ተማሪዎች በፕሮፖዛል አዘገጃጀት ዙሪያ ከጥቅምት 30 እስከ ህዳር 01 ቀን 2015 ዓ.ም ሲሰጥ የነበረዉ ወርክሾፕ ስልጠና በዛሬዉ ዕለት በስኬት ተጠናቀቀ፡፡
በስልጠናዉ የምርምር ርዕስ መረጣ እና አዘገጃጀት እንዲሁም አቀራረፅ (ፎከስ ኤሪያ) ፤ የመግቢያ ፤ ስቴትመንት ፕሮብሌም ፤ የምርምሩ መሰረታዊ አላማዎች፤ የምርምሩ ጥቅምና ስፋት ወይም ይዘት፤ሊትሬቸር እንዴት እንደሚፃፍ ፤ የሜቶዶሎጂ አዘገጃጀት ፤ የስራ እቅድ እና በጀት፤ በሶፍትዌር የታገዘ የሪፈረንስ አፃፃፍ እንዲሁም የዩኒቨርሲቲዉን የፕሮፖዛል ፎርማት ማላመድ የሚሉት በስልጠናዉ ወቅት ከተዳሰሱት ዉስጥ ዋና ዋናዎቹ ናቸዉ፡፡
በመጨረሻም በቀብሪደሃር ዩኒቨርሲቲ የምርምር፣ ህትመት እና የቴክኖሎጂ ሽግግር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር የሆኑት አቶ መሀመድ አብዲ ዋሊ እና የድህረ ምረቃ ጥናት ዳይሬክቶሬት ምክትል ዳይሬክተር የሆኑት አቶ አብዲሪሳክ ጣሂር ለስልጠናዉ መሳካት ጉልህ ሚና ለነበራቸዉ አካላት በሙሉ ላቅ ያለ ምስጋና በማቅረብ፤ ለተሳታፊዎችም ከስልጠናዉ ያገኙትን እዉቀት ወደ ተግባር በመቀየር ፕሮፖዛላቸዉ ሲፅፍ(ሲያዘጋጁ) ይህንን ተግባር ተኮር ስልጠና ከግምት እንዲያስገቡ ገልፀዉ ፤ የስልጠናዉ መርሀግብርም ለአሰልጣኞችና ለሰልጣኞች ሰርተፍኬት በመስጠት በመልካም ሁኔታ ተጠናቋል፡፡
ህዳር 01፤2015
ቀብሪደሃር ዩኒቨርሲቲ፤ ቀብሪደሃር ኢትዮጵያ