የቀብሪ ደሃር ዩኒቨርሲቲ የስራ አመራር ቦርድ የ2015 ዓ.ም 2ኛ መደበኛ ስብሰባ ተካሄደ

የቀብሪ ደሃር ዩኒቨርሲቲ የስራ አመራር ቦርድ የ2015 ዓ.ም 2ኛ መደበኛ ስብሰባ ያካሄደ ሲሆን ቦርዱ በ2 አጀንዳዎች ላይ ተወያይቶ ውሳኔዎችን አስተላልፏል።

የስብሰባው አጀንዳዎች፡-

1ኛ. የ2015 በጀት ዓመት የዝግጅት ምእራፍ የሆነውን የ1ኛ ሩብ ዓመት እቅድ አፈፃፀም ገምግሞ ማጽደቅ

2ኛ. በዩኒቨርሲቲው ትኩረት መስክና ተልዕኮ ሪፎርም ላይ ተወያይቶ የመጨረሻ አስተያየት መስጠት ሲሆኑ በስብሰባው ላይ ሁሉም የስራ አመራር ቦርድ አባላት እንዲሁም የዩኒቨርሲው ፕሬዝደንት፣ የአካዳሚክ ጉዳዬችና ምርምር ም/ፕሬዝደንት እና የአስተዳደርና ልማት ም/ፕሬዝደንት በተሳታፊነት በመገኝት በሰፊው ውይይት ተደርጎበት የሩብ አመቱን ሪፖርት በሙሉ ድምጽ በማጽደቅ እንዲሁም በዩኒቨርሲቲው የትኩረት መስክ ላይ የመጨረሻ አስተያየት በምስጠት ለትምህርት ሚኒስቴር እንዲላክ በሙሉ ድምጽ በመወሰን ስብሰባው ተጠናቆዋል።

ቀደዩ

ህዳር 1/2015 ዓ.ም