በዛሬዉ እለት ነሃሴ 28/ 2013ዓ.ም የቀብሪደሃር የሴኔት ስብሰባ የተካሄደ ሲሆን በተለያዩ አጀንዳዎች ላይ በስፋት ውይይት ከተካሄደ በኋላ የሚከተሉት 4 (አራት) ውሳኔዎች ተላልፈዋል፡-
1. በሬጅስትራር እና አልሙናይ ዳይሬክቶሬት የቀረበዉን የቀብሪ ደሃር ዪኒቨርሲቲ ሁለተኛ ዙር የ2013ዓ.ም ተመራቂ ተማሪዎች ወንድ 520 ሴት 301 በድምሩ 821 ተማሪዎች እስታተስ በማዳመጥ በሙሉ ድምፅ እንዲመረቁ አጽድቋል፡፡
2. በ2014 ዓ.ም በቀብሪደሃር ዩኒቨርሲቲ የሚከፈቱ 14 የመጀመርያ ዲግሪ ፕሮግራሞችን በሙሉ ድምፅ እንዲከፈቱ ያፀደቀ ሲሆን 3 የሁለተኛ ዲግሪ ፕሮግራሞችን በሴኔት ደረጃ በማፅደቅ ወደ ዩኒቨርሲቲዉ ቦርድ እንዲተላለፉ ዉሳኔ ተሰጥቷል፡፡
3. በተቋማዊ ለዉጥ ማጎልበቻ እና ማሻሻያ ዳይሬክቶሬት ተዘጋጅቶ የቀረበዉን የአካዳሚክ ፕሮግራም መክፈቻና ማሻሻያ መመርያ ደንብ ላይ ግምገማ በማድረግ እንዲፀድቅ ዉሳኔ ተሰጥቷል፡፡
4. በድህረ ምረቃ ትምህርት ቤት የቀረበዉን የድህረ ምረቃ ትምህርት መተዳደሪ ደንብ ግምገማ በማድረግ አፅድቋል፡፡
ቀደዩነሃሴ 28/2013ዓ.ም