የቀብሪ ደሃር ዩኒቨርሲቲ መደበኛ የሴኔት ስብሰባ ተካሄደ

የቀብሪ ደሃር ዩኒቨርሲቲ መደበኛ የሴኔት ስብሰባ የተካሄደ ሲሆን በስብሰባው ላይ ሁሉም የዩኒቨርሲቲው ከፍተኛ አመራርና የሴኔት አባላት በሙሉ የተገኙ ሲሆን ከስር በቀረቡት ሰባት አጀንዳዎች ላይ በሰፊው ውይይት በማድረግ ውሳኔውችን አስተላልፎዋል።

የስብሰባው አጀንዳዎች፡-

1ኛ. በመካሄድ ላይ ያለውን የመማር ማስተማር ስራ መገምገም

2ኛ. በዩኒቨርሲቲው የተዘጋጀውን የተማሪዎች መማሪያ መጽሀፍ/ሀንድቡክ ማጽደቅ

3ኛ. በዩኒቨርሲቲው የተዘጋጀውን የተማሪዎች የመውጫ ፈተና መመሪያ ማጽደቅ

4ኛ. በዩኒቨርሲቲው የተዘጋጀውን የምርምር ፖሊሲ እና መመሪያ ማጽደቅ

5ኛ. በዩኒቨርሲቲው የተዘጋጀውን የማህበረሰብ ተሳትፎ ፖሊሲ እና መመሪያ ማጽደቅ

6ኛ. የዩኒቨርሲቲውን የምርምር ስራ ማበረታቻ መገምገምና መከለስ

7ኛ. የሁለት መምህራን/ሌክቸረር ወደ ረዳት ፕሮፌሰርነት ማጽደቅ ሲሆን ሰኔቱ በሰፊው ውይይት በማድረግ ሁሉንም አጀንዳዎች እንዲሁም የሁለቱን መምህራን (ረ/ፕሮፌሰር ላታሞ ላሜሶ እና ረ/ፕሮፌሰር አብዶ ውዳድ) ረዳት ፕሮፌሰርነት በሙሉ ድምጽ በማጽደቅ ተጠናቋል።

ቀደዩ

ታህሳስ 27/2015 ዓ.ም